የኢትዮጵያ ማህበራዊ አገልግሎት ኮሚቴ
ዓለም አቀፍ የሴቶችን ቀን ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ ማህበራዊ አገልግሎት በሴትች ላይ ያለውን በደልና ጭቆና ለመቀነስ ብሎም ለማጥፋት የተደረገ ውይይት መጋቢት፲፮ ፪ሺ፭ (march 23, 2013) NY USA የዕለቱ ውይይት በወ/ሮ ዘውዲቱ ፍስሐ አጭር መግቢያ ንግግር ተከፈተ በንግግሩ ላይም ይህ የሰራትኞች መብት ማጣት በመካከለኛው አረብ ሀገሮች ማለትም በተቀባዮቹ ሀገራት የቆየ ችግር ነው። ሁሉም ይናገራል ይጮሃል ወይንም መንግስትን ይቃወማል ይህ ድግሞ ችግሩን እስካሁን አልፈታውም አይፈታውም ስለዚህ አቅም ያለው ባቅሙ ሌላው በሙያው በመድጋገ ፍ ሁላችንም አንድ ላይ በመሆን ለችግሩ መፍትሄ አንሻ አሮሮው ብሎም ወሬው ይቅር ወደ ለውጥ እንሂድ በተልይ አሜሪካን ነዋሪ የሆነው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከአሜሪካን ወንድሞቻችን ጋር በመሆን በማለት ቤቱን ለውይይት ጋበዙ። ከዚያም በመቀጠል ወ/ት ከእብነሽ ግርማ (New vision children foundation)የዕለቱ ፕሮግራም መሪ የተጋበዙትን ተናጋሪ እንግዶችን ወደ መድረክ በመጋበዝ ለጉባኤው አስተዋወቁ ።